ወያኔ የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በቺካጎ ሊቋቋም በእቅድ ላይ መሆኑ ተገለጸ

ወያኔ የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በቺካጎ ሊቋቋም በእቅድ ላይ መሆኑ ተገለጸ

 ለ26 አመታት ኢትዮጵያውያኖችን እና ሌሎች አገር ዜጎችን በመርዳት የሚታወቀውን አንጋፋ ኮሚኒቲ አፍርሶ በወያኔ አባሎች ሊመራ የሚችል ኮሙኒቲ ለማቋቋም በቺካጎ የሚኖሩ የወያኔ አባላቶች ዝግጅታቸውን መጀመራቸውን ተገልጾአል ።በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት የወያኔውች መጮሂያ ግቢ እየተባለ በሚጠራው የራስ ዳሸን ምግብ ቤት በተደረገው ውስጥ ባደረጉት ስብሰባ ከፍተኛ የገንዘብ በጀት በመመደብ ትልቅ ዝና እና ክብር ያለውን እንዲሁም በቺካጎ አስተዳዳሪዎች ወደር ያለተገኘለት ኮሙኒቲ ተብሎ የተመሰከረለትን ኮሙኒቲ ለማፍረስ እና በራሳቸው የሚመራውን ማህበር ለማቋቋም ትግላቸውን ቀጥለዋል፣ይህንን ጉዳይ ግን ቀዳሚው እና የሃያ ስድስት አመት አንጋፋ የሆነው ኮሙኒቲ ጉዳዩን ሊደርስበት አልቻለም ይህ የወያኔ አባላቶች በሴብቴምበር 2 በራስዳሸን ሬስቱራንት ስብሰባ ያደርጋሉ  ።

በሳለፍነው ሁለት አመታት የራሱን ህንጻ በመግዛት የመጀምሪያው በሰሜን አሜሪካም ሆነ አውሮጳ ካሉት ኮሙኒቲዎች ውስጥ የሃገሩን ቅርስ ለማስተዋወቅ የባህል ማእከል ወይንም ሙዚየም ያለው ብቸኛ ኮሙኒቲ መሆኑ ይታወቃል  በሌላም በኩል አለም አቀፍ ስደተኞችን እና ሌሎች የራሱን ዜጎች በስደትም ላይ ያሉ ሆነ በትምህርታቸው ልቀው የወጡ ተማሪዎችን እንደዚሁም በተለያዩ የኮምፒዩተር ኢንጂኒየሪንግ ሰልጥነው የማጠናከሪያ የሙያ ስልጠና እንዲያገኙ ከሃገር ቤት ድረስ ስፖንሰር በማድረግ ከፍተኛ ድጋፍ ለወገኖቹ ሲያደርግ  በሌላም በኩል በሰሜና አሜሪካ  እንግዳ ለሚሆኑ ወገኖቹ ስራን በማፈላለግ በአሜሪካ ተወልደው ያደጉትን ህጻናት ቋንቋቸውን እንዲያውቁ እና በእረፍት ጊዜዎቻቸው የማጠናከሪያ የጥናት ፕሮግራም እንዲያደርጉ ጥረት ሲያደርግ ቆይቶአል አሁንም ከፍተኛ የሆነ የጀርባ አጥንት መሆኑ ተመስክሮለታል ። ይህንን ስራ ሲሰራ ግን ከማንኛውም ወላጆች የገንዘብ ድጋፍ አይጠይቅም ።በተለይም ረዳት የሌላቸውን እና በድንገተኛ አደጋ ህይወታቸው ያለፉ ዜጎቹን ገንዘብ በማሰባሰብም ሆነ ከእራሱ የባንክ አካውንት በማውታት ስርአተ ቀብራቸውን በማስፈጸም ጉዳይ ወይንም አስከሬኖቻቸው ወደ ትውልድ መንደራቸው እንዲሻገር በማድረግ ከፍተኛውን ድርሻ ሲወጣ የቆየውን ይህንን ድርጅትን ለማፍረስ የሚደረገው ጥረት እውነትም አላዋቂነትን ያሳያል ተብሎአል ። በተወሰኑ ብሄሮች ብቻ ሊመራ የሚችል ኮሙኒቲ ለማቋቋ ታሪካዊ ስራን የሰራ ድርጅትን ከማፍረስ ይልቅ ተባብሮ ሃገርን እና ወገንን ለመርዳት ቢጥሩ መልካም ነበር ፣ነገር ግን ታሪክን ባህልን ዘርን በማጥፋት የሚታወቀው ኢሃዴግ ወያኔ እና ተከታዮቹ የዚህ ሰለባ መሆናቸው ግልጽ ነው ።ይህንን ማህበር እንዳይቋቋም የማለዳ ታይምስ የሰሜና አሜሪካ  ዋና አዘጋጅ ዘላለም ገብሬ በመላው አለም ለሚገኙት ወገኖች የፒትሽን ዝግጅት በኦንላይን ላይ በማዘጋጀት ላይ ይገኛል በቅርቡ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ይገለጻል ።

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close