ሰበር ዜና መለስ ዜናዊ መሞታቸውን የሃገሪቱ ሚዲያ በዛሬው እለት ገለጹ ።

ለረጂም  ወራት ሲያወዛግብ የነበረው የጠቅላ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በህይወት የመኖር እና ያለመኖር ጉዳይ ዛሬ በኢትዮጵያ መንግስት በሚተዳደረው የኢዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያ ለአገሪቱ ህዝቦ መግለጹ ታወቀ ።  በአሁኑ ሰአት በሃገሪቱ መረጃ  ማእከል መግለጫ እየተሰጠ ይገኛል ..ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ሃገሪቷን በጊዜአዊ አስተዳደር እንደሚመሯት የሃገሪቱ ሚዲያ ገልጿል ።በዚህ ሳምንት  በኢትዮጵያ ውስጥ ከፈተኛ ውጥረት  ነግሶባት የነበረ ቢሆንም በትላንትናው እለት አቶ በረከት ስምኦን ወደ እንግሊዝ አገር እምደተጓዙ  መረጃዎቻችን የጠቆሙ ሲሆን በዚህ መረጃ መሰረትም የህወሃት አባላቶች በሙሉ  ከአቶ በረከት እና ሰብሃት ነጋን  በኩል ተሰልፈዋል ። በአቶ ሰብሃት ነጋን  በኩል አቶ በረከት ስምኦንን ወደ ዘብጥያ ለማውረድ ከ እነ አቶ ጌታቸው ጋር ሴራቸውን እየጠነሰሱ እንደሚገኙ ሲገለጽ በአቶ በረከት ስሞን በኩል ደግሞ  ያለአግባብ ስልጣናችንን ተጋፉን በሚል ምክንያት አቶ ሰብሃት ነጋን ከስራቸው ለማገድ ችለዋል ።

የማለዳ ታይምስ ዘጋቢዎች የአቶ መለስ ዜናዊን የስራተ ቀብር አስመልክቶ በሰፊው ዘገባ ይዘው ለመቅረብ ይሞክራሉ ።ከነገው እለትም  ጀምሮ የሃገሪቱ ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብም ትእዛዝ ከሚንስትሮች መስሪያቤት ተላልፏልመለስ ዜናዊ መሞታቸውን መንግስት አምኖ ይፋ አደረገ ።መንግስታዊው ኢቲቪ ዛሬ ባቀረበው ዘገባ መለስ ዜናዊ ትላንት ሞተዋል። አቶ በረከት መለስ ከአዲሱ ዓመት በፊት ይመጣሉ ሲሉ አቶ ስብሃት መለስ በቤተ መንግስታቸው አገር ይመራሉ የተባለውን ሀሰት መሆኑን ለኢሳት በሰጡት ዘገባ ማረጋገጣቸው ይታወሳል።
ኢሳት ከአይሲጂ ያሉ ምንጮቹን በመጥቀስ መለስ መሞታቸውን አስቀድሞ መግለጹ ይታወሳል።የመለስን ሞት ተከትሎ ሰሞኑን የህወሃት ባለስልጣናት በውጭ እና በአገር ውስጥ ያሉ ደጋፊዎቻቸውን አለ ሲሉ የከረሙበትን ደግመው ለማስተባበል ይገደዱ ይሆናል።
አቶ በረከት መለስ ሞቷል የሚለውን ለማስተባበል ሕዝቡ ያምነናል ሲሉ ቢቆዩም ሕዝቡ ዕውነት አለመናገራቸውን ስለሚያውቅ በከፍተኛ ጥርጣሬና ስጋት ውስጥ መቆየቱ ይታወሳል።
ህብር ሬዲዮ ላስ ቬጋስ  በዚህ ላይ ሰፊ ዘገባ ይዞ በሚቀጥለው ሳምንት ይቀርባል ።

መለስ ዜናዊ

መለስ ዜናዊ

መለሰ ዜናዊ (የትውልድ ስማቸው ለገሠ ዜናዊ አስረስኢትዮጵያ የፖለቲካ ሰው ናቸው። በአድዋ ትግራይ በ(ሚያዝያ 30 ቀን 1947 ዓ.ም. ተወለዱ። ከ1987 አንስተው በኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን በከፍተኛው የአመራር ቦታ ላይ ነበሩ። የኢህአዴግና የሕውሓት ሊቀመንበር በመሆን ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ 2004 ቆይተዋል።

ኣቶ መለስ ዜናዊ ኣባታቸው የትግራይ ተወላጅ ሲሆኑ በእናታቸው በኩል ደግሞ ኤርትራዊ ናቸው፡፡

ማውጫ

[ይደበቅ]

አቶ መለስ የሚመሩት ሕውሓት የኮሎኔል መንግስቱ ኅይለ ማርያምን አምባ ገነናዊ መንግስት በትጥቅ ትግል ሲታገሉ ከነበሩ ድርጅቶች አንዱ ነው። አቶ መለስ የሕወሓት አመራር ኮሚቴ መሪ ሆነው በ1971 ተመረጡ ቀጥሎም በ1975 የድርጅቱ ማእከላዊ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆኑ። የደርግ መንግሥት ከወደቀም ጀምሮ የሕውሓትና የኢህአዴግ ሊቀ መንበርም ናቸው። ኢህአዴግ የአራቱ ፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም የኦሮሞ፣ የአማራ፣ የትግራይና የደቡብ ሀዝቦች ብሔር ውህደት ነው። ወደ ስልጣን ሲመጡ በጊዜው ላቋቋሙት ጊዜያዊ መንግስት ፕረዚዳንት ሆነው ካገለገሉ በሗላ 1985 ለመጀመሪያ ጊዜ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነውም ተመረጡ። በጊዜው የፕረዚደንትነቱን ቦታ የተረከቡት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ናችው። በመቀጠልም አቶ መለስ ከባድ ውዝግብ ባስነሳው የ1997 ግንቦት ምርጫ አሸናፊ ሆነው ለሁለተኛ ጊዜ በስልጣን ላይ ይገኛሉ። ጠ/ሚ መለስ በመላው አለም በአምባገነንነት ከሚታወቁ መሪዎች አንዱ ናቸው።በስልጣን ላይም 21 ዓመታት በላይ ቆይተዋል።ወደ ስልጣን አመጣጥ

የሽግግር መንግስታቸው

የመንግስቱ ኃይለ ማርያምን መሸነፍ ተከትሎ አዲስ አበባን የተቆጣጠረው ኢአሓዴግ መንግስትን ሲያቋቁም ብሔረሰቦችን መሰረት ባደረገ ፓርላማ ስለነበረ ቀድሞ ያልታየና አዲስ ስለነበረ ብዙዎቹን ግራ አጋብቶ ነበር። የሽግግሩ መንግስት በጊዜው ኢህአዴግ ያሰባሰባቸው ድርጅቶች ብቻ ጎልቶ የታዩበት ስለነበረ አሰባሳቢነት የመጡ ስለነበር ከትችትና ከተቃውሞ አላመለጠም።

የኢህአዴግ ደጋፊዎች

በአምባ ገነኑ ደርግ ስር ተጨቁኖ ለነበረው ድሃ ኢትዮጵያዊ የኢህአደግ ወደ ስልጣን መምጣት ከ«የምስራች» ና ሌላ አማራጭ ስላልነበር የኢሕአዴግን መንግስት ሕዝቡለመቀበል ተገደደ ። ከዚህም የተነሳ ኢህአዴግ ይህ ነው የተባለ ተቃውሞ አልገጠመውም። ኢሕአዴግን ሲረዱ የነበሩ የአረብና የምዕራባውያን መንግስታት ከጎንህ አለን በማለት በብዙ ትግል ስልጣን የተቆናጠጠውን ኢህአደግን በሁለት እግሩ አንዲቆም አስችለውታል። የአቶ መለሰ ዚናዊ መንግስት የታገለለትን ዓላማ ስቶ ዲሞክራሲንበማፈን የነጻ ፕሬስ አፈና በማካሄድና የብአዊ መብት ረገጣ ስላበዛ ብዙ የምዕራባዊያን ድጋፍና ከማጣቱም በላይ የብዙ ሺ ኢትዮጵያዊያን ለስደት ዳርጎአል። ሆኖም ዓለም አቀፉን ሽብርተኛ ለመታገል ቃልበገቡት መሰረት ሱማሌን በመውረሩ ምክንያት በጆርጅ ቡሽ የምትመራ አሜሪካ ቀንደኛና ዋነኛ የኢህአዴግ ደጋፊ ሆና ቀርታለች።

የኢህአዴግ ተቃዋሚዎች

መለስ ዜናዊ ከአጼ ኃይለ ስላሴ ሽልማት እንደተቀበለ (1964 ዓ.ም.)

ምንም እንኳ በደርግ የግፍ አገዛዝ የተማረረው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ኢህአዴግን ለመቀበልና አብሮ ለመስራት ወደ ኋላ ባይልም ውሎ ሲያድር ግን በኢህአዴግ የአገር ውስጥ ፖሊሲ መከፋቱ አልቀረም። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ብሎ ራሱን የስየመው ቡድን ከኢህአዴግ ጋር በመቃቃሩ ራሱን ከፓርላማውና ከካቢኔው አግልሎ ወደ ትጥቅ ትግሉ ተመለሰ።

ጠ/ሚ መለስ የኤርትራን የመገንጠል ጥያቄ ያለምንም ማንገራገር መፍቀዳቸው ብቻ ሳይሆን ሁሉም ብሔረሰብ እንዲገነጠል የሚያስችለውን አንቀጽ በሕገ መንግስታቸው በማካተታቸው በተለይ በምሁራን ዘንድ የከረረ ተቃውሞ አስነስቶባቸዋል። ሁሉም በክልሉ በቋንቋው ይማር የተሰኘው ፖሊሲያችውም በብዙዎች ዘንድ ጥርጣሬና መከፋፈልን በመፍጠሩ በሀገርና ከሀገር ውጭ በተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፎች ተካይዶባቸዋል።

በ1997 አጋማሽ ጠቅላላ ምርጫ ሲደረግ ከተለያዩ የፖለቲካ ህቡዕ ፓርቲዎች የተውጣጣ ቅንጅት የተሰኘ ጥምር የፖለቲካ ፓርቲ እንደ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ተወዳደረ። በውጤቱም የዓለም ታዛቢዎች በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ ከመቶ 97 እጁ መራጭ የተቃዋሚውን ፓርቲ ቅንጅትን መረጠ። በውጤቱ የተደናገጠው የአቶ መለስ መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ የአዲስ አበባን ፖሊስ በፌዴራል ቁጥጥር ስር አዞረ። የአዲስ አበባ ምክር ቤትንም በኦሮሚያ መስተዳደር ስር እንዲተዳደር አዲስ ድንጋጌ አወጣ።

ይሁን እንጂ ብዙም ገለልተኛ ታዛቢ በሌለበት ከአዲስ አበባ ውጪ ኢሕአዴግ 90 በመቶ ማሸነፉ ስለታወጀ ተቃዋሚዎች አድልዎ ተደርጎብናልና ምርጫው እንደገና ይጣራ ብለው ለከፍተኛ ፍርድ ቤት የክስ ማመልከቻ በማስገባታቸው ማጣሪያ ተካሄደ። ተቃዎሚዎች በጠቅላላው የምርጫ ውጤት ባለመስማማታቸው ያሸነፉበትን የፓርላማ ወንበር ባለመቀበል የገዢው ፓርቲ በበላይነት ከተቆጣጠረው ፓርላማ ራሳቸውን አገለሉ።

ሚሥስ አና ጎሜዝ የተባሉ የአውሮፓ ታዛቢ ቡድን መሪ ምርጫው አድልዎና ጫና እንደነበረበት ለዓለም ሕዝብ ምስክርነታቸውን ተናገሩ። አብዛኛዎቹ ታዛቢዎች (አፍሪካ ሕብረት አና የጂሚ ካርተርማእከል) ምርጫው በኢትዮጲያ ከተካሄዱ ምርጫዎች በጣም የተሻለ መሆኑን መሰከሩ። በሺ የሚቆጠሩ የቅንጅት ደጋፊዎች በዋና ዋና ከተማዎች በመውጣት ሰላማዊ ሰልፍ በቁጣ በሚገልጹበት ጊዜ ቁጥሩ በርካታ የሆነ ሕዝብ በፖሊስ በቀጥታ በተተኮሰ ጥይት ሕይወቱን አጥቶአል። የአቶ መለስ መንግስት አብዛኛዎችን በህዝብ የተመረጡ የቅንጅት ፓርቲ አባላትንና በሺህ የሚቆጠሩ አባላትን ባገር ክህደት አና መንግስትን ለመገልበጥ በመሞከር ከሰሳቸው። 2 ዓመት በፈጀ የፍርድ ሂደትም ፍርድ ቤቱ የቅንጅት መሪዎችን አገርን በመክዳት ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው አገኛቸው ። ይሁን እንጂ ሁሉም የ ቅንጅት መሪዎችና አብዛኛው ደጋፊ አባላት ጥፋታቸውን አምነው ይቅርታ በመጠየቃቸው ከእስር ነጻ ወጡ። በ2004 አመት ምህረት በአሜሪካ በተካሄደው የአለም አቀፍ የባለ ሃብቶች ስብሰባ  በጋዜጠኛ አበበ ገላው ድንገተኛ የነጻነት ጥያቄ ከመደንገጣቸውም በላይ በመታመማቸው ብዛት ድንጋጤአቸው ለህልፈተ ሞት አድርሶአቸዋል።በ57 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close