መለስ ዜናዊ መሞቱን መንግስት አምኖ ይፋ አደረገ ።መንግስታዊው ኢቲቪ ዛሬ ባቀረበው ዘገባ መለስ ዜናዊ ትላንት ሞቷል። አቶ በረከት መለስ ከአዲሱ ዓመት በፊት መለስ ይመጣሉ ሲሉ አቶ ስብሃት መለስ በቤተ መንግስታቸው አገር ይመራሉ የተባለውን ሀሰት መሆኑን ለኢሳት በሰጡት ዘገባ ማረጋገጣቸው ይታወሳል።

ኢሳት ከአይሲጂ ያሉ ምንጮቹን በመጥቀስ መለስ መሞታቸውን አስቀድሞ መግለጹ ይታወሳል።የመለስን ሞት ተከትሎ ሰሞኑን የህወሃት ባለስልጣናት በውጭ እና በአገር ውስጥ ያሉ ደጋፊዎቻቸውን አለ ሲሉ የከረሙበትን ደግመው ለማስተባበል ይገደዱ ይሆናል።

አቶ በረከት መለስ ሞቷል የሚለውን ለማስተባበል ሕዝቡ ያምነናል ሲሉ ቢቆዩም ሕዝቡ ዕውነት አለመናገራቸውን ስለማያውቅ በከፍተኛ ጥርጣሬና ስጋት ውስጥ መቆየቱ ይታወሳል።

ህብር ሬዲዮ ላስ ቬጋስ

Advertisements