የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ድል ተቀዳጀ የሱዳን አቻውን 2ለ0 አሸነፈ

በዛሬው እለት ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የ እግርኳስ ጨዋታውን ከአቻው ቡድን ከሱዳን ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቡድን አቻውን 2ለ0 አሸንፏል ይህ ድልእና ለዚህ ዋንጫ መድረሱ  ከረጅም ዘመን በኋላ የመጣ መሆኑን መላው የኢትዮጵያን ህዝብ አስደስቷል በጨዋታው ከፍተኛ ፉክክር የታየበት ቢሆነም በሳላሃዲን እና  በአዳነ ግርማይ በተቆጠሩ ሁለት ግቦች ለድል መብቃታቸው ተገልጾአል ።

ከዚህ አፍሪካ ውድድር በኋላ በሊቢያ ይደረጋል ተብሎ የነበረው እና በአሁን ሰአት በሳውዝ አፍሪካ እንዲከናወን የተደረገው ይሄው ውድድር  የአሸናፊዎች አሸናፊ ሆኖ የሚቀርበውን ቡድን በብራዚል አለም አቀፍ ዋንጫ ላይ ይሳተፋል ተብሎ የሚጠበቅ ቡድን ይሆናል ለዚህም ዝግጅት ሃላፊ ቡድኖቹ ከፍተኛ የሆነ ውጤት የሚጠበቅባቸው ሲሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቀጣዩን ዙር ለማለፍ ከፍተኛውን ትግል ያደርጋል ተብሎም ይጠበቃል ።

እንደአንዳንዶች ገለጻ ከሆነ የብሄራዊ ቡድናችን እየገሰገሰ ይሄድ እና መጨረሻ ላይ ወደ ሽንፈት ይዳረጋል ይህ ደግሞ የአሰላለፍ ስልታቸው ተመሳሳይ ስለሚሆነ እና ብዙም ተጨዋቾችን ስለማያሳትፉ ፣ተጨዋቾች በደከሙ ቁጥር ለመቀየር የሚያስችላቸውን ያህል አቅም ስለሌላቸው ውጤት ላይ ዜሮ እንሆናለን እኛ ለ31 አመታት ዋንጫ ናፍቆናል ስማችንን ማስጠራት የምንፈልገው በጥሩ ሁኔታ መሆን ይገባዋል ሲሉ አሁን ግን የፌደሬሽኑ የውስጥ ለውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ገንዘቦች ዘረፋ አቁሞ  ከአለም አቀፉ እግርኳስ ፌደሬሽን በየአመቱ የሚሰጠውን በሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ለክለቡ ማጠናከሪያ ቢያውለው እኛ ወደ ኋላ አንቀርም ያሉት የቀድሞው የመድን እና ንግድ ባንክ ተጨዋች የነበሩት አቶ ዘነበ በዚሁ ከቀጠሉ ግን ስለ ብሄራዊ ቡድኑ ያላቸውን ስጋት እና የፌደረሽኑ እጣ ፈንታ ምን ልሆን እንደሚችል ጠቁመቅዋል። በሌላም በኩል  በፌስ ቡክ አበበ ቶላ (አቤቶክቻው ) እንዲህ ሲል የገለጸ ሲሆን “ የኢትዮጵያ እግርኳስ ቡድን አሸነፈ ሳልሳዲን እና አዳነ ግርማይ አንዳንድ ጎል አስቆጠሩ ዛሬ ጥቅምት 4 በተደረገው ወሳኝ ጨዋታ ወሳኝ የሆኑ አንድ አንድ ጎል አግብተው ኢትዮጵያን ከ31 አመታት በዋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ አምጥተዋታል።
የኢቲቪ ጋዜጠኞች “ይሄ ውጤት ለሟች መለስ መታሰቢያ ነው” ሲሉ ሰማሁ! አልገባኝም…! መለስ የኢትዮጵያ ፉት ቦል ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ነበሩ ነው… ወይስ ምንድነው…!? ይህንን የጋዜጠኞቹን ንግግር ሚዛናዊ ለማድረግ በርካታ ኢትዮጵያውያን “አቶ መለስ እንኳንም ሞቱ ለካስ እስከዛሬ እርሳቸው ነበሩ የቋጠሩብን” ሲሉ መናገራቸውንም እናገራለሁ! በ21 አመት ቆይታቸው አንድ ስታድየም እንኳ ላልገነቡ ሰውዬ ይህንን ውጤት መታሰቢያ ማድረግ ምን ይሉታል… ወይስ “ይብላኝ ለርስዎ እኛስ አሸነፍን!” ማለት ይሆን!
ለማንኛውም እንኳን ደስ አለን!” በማለዳ ታይምስ አዘጋጅ ደግሞ ይህንን አይነት ምላሽ የሰጠው ሲሆን ያለፈውን የአቶ መለስን ንግግር ለማየት የሚያጭር ሃሳብ እንደሆነ እና እሳቸው ለእግር ኳስ ክለብም ሆነ ለሩጫ ጊዜም ሆነ ፍላጎት እንደሌላቸው የሚታወስ ነው ለዚህም ሲሉ በሩጫው በኩል የተናገሩትን ምንም ሳናስቀር የምናቀርበው ሲሆን በሩጫው በኩል ሃይሌ ገብረ ስላሴን ብቻ የተናገሩትን ማስታወስ ይቀላል “ እግር ጭንቅላት አይሆንም “ሩጫ ስለሮጠ ያስባል ማለት አይደለም ደደብ በሉት ይመስላል ቀጥታ ንግግራቸው በ እንዲህ አይነት የፌዝ ዘመን ላለፉት አስተዳደር መታሰቢያ ተብሎ ሰወሳላቸው የሚያሳፍር ተግባር ነው ለዚህም እውነትም ኢቲቪ ታውሯል እስኪ ወደ ማህደራቸው ገባ ይበሉ እና የአቶ መለስን የስፖርት አፍቃሪነት የሚያመለክተውን እንዲመለከቱ እንጋብዛቸው ?በተለይም በደርግ የአስተዳደር ዘመን ስታዲየም ይሰራል ተበሎ የተቀመጠውን ገንዘብ አቶ መለስ እጅ በገባበት ወቅት ጊዜ “ይህንን ገንዘብ ማዳበሪያ እንገዛበታል ስታዲየም አስገንብተን የከብት ማጎሪያ አይሆንም ተጨዋቾች የሚባሉትም እግር የላቸውም ሲሉ ግልጽ ብወጣ ስድብ ሲናገሩ አልነበረም ዛሬ ለእግርኳስ እድገት አንም ላልጣረ አቆርፋዳ እንደገና ማስታወሻ ብለው ሲሉ ምን ማለታቸው ይሆን እስከዛሬ የቋጠሩት ፌደሬሽኑን ለመግደል አልነበረም ተጨዋች ማሳጣት ፈልገው አልነበረም?ከ40 አመታት በላይ ያገለገለው እስታዲየም ሳይታደስ ዛሬም ድረስ የሚፈነጭበት በእርሳቸው ትልቅ ትግል ይመስለኛል

Maleda Times

 

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close