ማህበረ ቅዱሳን “አክራሪዎች” ወይስ ህግ አክባሪዎች?

በታምሩ ገዳ

አቶ መለስ ዜናዊ በቀርቡ ዙሪያ ገባውን በደጋፊዎቻቸው ከተሞላው ፓርላማቸው   ፊት ቀርበው  አገሪቱ ውስጥ “ተከስቷል” ወይም “እየተከሰተ ነው”  ስላሉት የአክራሬነት  እንቅስቃሴ    ዙሪያ ትንታኔ መስጠታቸው  ይታወሳል፡፡በዚህ ማብራሪያቸው  ላይ በኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ  ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ስር የነበረው እና በቅርቡ በጠቅላይ ቤተክህነት ስራ አስኪያጅ  ስር  የሆነው እና  በአገር ወስጥ ሆነ በውጪ አገር በብዙ ሺዎች  የሚቆጠሩ  ጠንካራ ደጋፊዎች አንዳሉት የሚነገርለትን   የማህበረ ቅዱሳን  ስምን  “በንጽጽርነት ” ጠቅሰዋል፡፡ ይህ  አገላለጻቸው በበርካታ ምእመናን  ዘንድ ሰሞኑን  ከፍተኛ ቅሬታን እና  ሃዘኔታን የጫረ  ሲሆን አንዳንድ ወገኖች ደግሞ  “ሊበሏት ያሰቧትን  አሞራ…. “ብለውታል፡፡   ለመሆኑ ማህበረ ቅዱሳን  እንማን ናቸው ?  የየትኛው የፖለቲካ ቡድን ድጋፊዎች   ወይም  ነቃፊዎች ናቸው ?  ማህበረ ቅዱሳን  ከሙስና ምን ያህል የጸዳ ነው ?  አውዛጋቢው የአቡነ ጳውሎስ ሃውልት እስከአሁን ድረስ ባለመፍረሱ ተጠያቂው ማን ነው?  ቤተከረስቲያኒቱ የምእመናን  እና የገንዘብ  ደሃ ሳትሆን  በአሁኑ ወቅት በርካታ የገጠር ቤተክርስቲያናት እና  ገዳማት ለምን ይፈርሳሉ?  የሚሉትን  እና በርካታ መሰል ጥያቄዎችን ጨምሮ  ይህ ጸሃፊ ለማህበሩ አባል እና የወንጌል መምህር  ለሆኑት  ለዲያቆን ብርሃኑ አድማስ  ነጻ እና የግል አስተያየታቸውን አንዲሰጡት  ቀደም ሲል ጥያቄ እቅርቦላቸው  ነበር ፡፡ የቃለምልልሱ ወቅታዊነቱን  እና ጠቃሜነቱን  ከግንዛቤ ውስጥ በማካተት ጸሃፊው ለአምባቢያን   እንደሚከተለው አቅርቦታል ፡፡ መልካም ንባብ ይሁንሎት ፡፡

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close