ለቤተክርስቲያን ስርአት ደንታ የሌለው «የጎረምሶቹ ጳጳሳት» …

ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በተስፋና በመልካም ሁኔታ ለእርቀ ሰላም ከፍተኛ ደረጃ ሰጥቶ በቀኖና ቤተክርስቲያን ምክንያት ለ21 አመታት ምእመናንን ከምእመናን ፣ ካህናትን ከካህናት ፣ አባቶችን ከአባቶች ያስከተለውን ልዩነት የሚያሰወግድ ውሣኔ ያሳልፋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የአዲስ አባው ሲኖዶስ ቁጥር ወደ ኋላ አይቆጠርም በማለትና በአብዛኛው ሲኖዶስ ለተባለው የቤተክርስቲያን የበላይ አካል በማይመጥን ተራ አጀንዳ ሲወያይ የሰነበተው የአገር ቤቱ ሲኖዶስ የአዲስ አበባን ከተማን ለአራት በመከካፋልና ለዘረፋ በማመቻቸት ይልቁንም በቤተ ክርስቲያን ሀብትና ንብረት ላይ የተካሄደውን ሰዘረፋ የቅዱሳን አበው ማረፊያ ስለሆኑት ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት በተለይም ስለ ዋልድባ ገዳም እንድም ሳይተነፍስ እንዲሁም ሲኖዶሱ በዋናና ለቤተክርስቲያን መንፈሳዊ እድገትና ጥንካሬ የሚረዱ፣ ቤተክርስቲያንም በአገራችን ተገቢ ሚናዋን እንድትጫወት የሚያደርጉ አጀንዳ ከመቅረጽና ከመወያየት፣ ጠቃሚ ውሳኔዎችንም ከማሳለፍ ይልቅ በአብዛኛው ተራ በሆኑና ሲኖዶስ ላይ ሳይደርሱ መፈታት ባለባቸው ጥቃቅን አጀንዳዎች ላይ ሲወያይ አብዛኛውን ጊዜውን ማቃጠሉ፣ የሲኖዶሱ አባላት የሚገኙበትን ምን ደረጃ ላይ እንደሆኑ ያሳየ ክስተት ሆኖ አልፏል ይህም ውሣኔ ብዙዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን እውነተኛ ልጆች ያሳዘነና አንገት ያስደፋ ሆኖ ተገኝቷል ይህም ተራ ውሣኔ በአፈ ቀላጤው ሕዝቅኤል አማካይነት፣ የሲኖዶሱ መግለጫ ተሰጥቷል፣ በአዲስ አበባ ከሚገኙት ሊቃነ ጳጳሳት መካከልም የተወሰኑት አባቶች በዚህ የልዩነት ታሪክ ላይ እንዳለን በሞት ማለፋቸው አሳዛኝ ሆኖ ሳለ፣ አሁን በሁለቱም ወገን በህይወት ያሉት ማስተካከል ሲገባቸው ፣ ህገቤተክርስቲያንን ያልጠበቀ፣ ቤተክርስቲያንን አንድ ሊያደርግ የሚይችል በህዝብና፣  በእግዚአብሄር ፊት ተወቃሽ የሚያደርግ ውሣኔ አሳልፏል

ሌላው ዕርቀ ሰላሙ እውን እንዳይሆን እንደ አንድ ትልቅ ዕንቅፋት የሆነው በቡድን ስምንት የጳጳሳት ቡድን መካከል የተፈጠረው የፓትርያርክ እንመርጣለን ውዝግብና በአቃቤ መንበር አባ ናትናኤል እርቅ መቅደም አለበት የሚለው ነው ለቤተክርስቲያን ስርአት ደንታ የሌለው «የጎረምሶቹ ጳጳሳት» የነ«አባ» ሳሙኤል ቡድን ለጵጵስና በሚገባ ቅድስና ውስጥ የሌሉና የጋብቻ ወግ በሌለውና ለመናገር በሚከብድ የቅድስና ችግር ውስጥ የሚገኙ ናቸው።    መቼስ «ጳጳስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ» ሆነና ነገሩ የሚጠይቅ አካል ጠፋ እንጂ፥ እንዲህ ባለው የስነምግባር ችግር ውስጥ እያሉ እንኳን ለሚመኙት ፕትርክና ይቅርና ከጵጵስናውም የሚሻሩ ነበሩ። ነገር ግን በኢትዮጵያ ውስጥ እነርሱ ከሕግ በላይ ስለሆኑ እንዲህ እየሆኑም ተከብረው ይኖራሉ። በአሁኑ ወቅት ከሲኖዶስ ስብሰባ ጋር ተያይዞ ቤተ ክርስቲያኗን እናሽከረክራለን የሚሉት እነዚሁ የጉድ ሙዳዮች መሆናቸው ሲታይ ደግሞ እግዚአብሄር ይህችን ቤተክርስቲያን እየተዋት ለመሆኑ ትልቅ ማሳያ ነው የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም። ለእነዚህ የጉድ ማህደሮች ባህሪያቸውን የሚገልጽ ስም እዚያው ቤተክህነት ውስጥ የወጣላቸው ሲሆን የሚጠሩትም መሠሪው አብርሐም አጭበርባሪው ሣሙኤል አታላዩ ሉቃስ አስመሳዩ ሕዝቅኤል በመባል ነው

ይህ በእንዲህ እንዳለ ብዙዎችን እያነጋገሩ ካሉት ነገሮች ውስጥ ስለ ቀጣይ ፓትርያርክ ምርጫ  እና እርቀ ሰላም ይገኙበታል ፤ ከሁለት ሳምንት በወያኔ ቁልፍ ባለሥልጣናት አማካኝነት መንግሥት የራሱን ሰው ለማሾም ግሩፕ ስምንት የሚባሉትን ÈÈሳትን በመጠቀም  ሰባት ሰዎችን የያዘ ቡድን በሚስጥር መመስረቱ ተሰምቷል ይህ ም ግሩፕ በእጩነት ካረባቸው ÈÈሳት መካከል ለወ/ሮ አዜብ ጎላ የቅርብ ዘመድ ነው የሚባለውና ከወያኔ ሠራዊት ጋር አብሮ አዲስ አበባ የገባው አባ ተከስተ የአሁኑ ሳሙኤል ሲሆን ሌላውደግሞ የአባ Èውሎስ የቅርብ ደጋፊ የነበረው አባ ገርጎርዮስ እንዲሁም አባ ሉቃስ ናቸው  በሌላ በኩል ወ/ሮ እጅጋየሁ የምታንቀሳቅሰው ቡድን በሊቀ ሊቃውንት እዝራ የሚመራው ሲሆን የራሱን ተጽህኖ ለማሳደርና ከመንግስት ጋር አብሮ ለመስራት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ፤  ሊቀ ሊቃውንት እዝራ በተለያዩ የአዲስ አበባ አብያተተክርስትያን ላይ ዘረፋ በማካሄድ እንደ ጥጃ ታስሮ በመፈታት የሚታወቅ አደገኛ ዘራፊ መሆኑን ይታወቃል

ሌላውን ደግሞ በቀጣይ የምናየው ይሆናል

 

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close