የባቢሎንቋንቋ

በዮሴፍ ሽፈራው(ጀርመን)

ሁለት ሺህ ዓመታት ስርዓቷን፣አንድነቷን ትውፊቷን ጠብቃ የቆየችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ካለፉት 20 ዓመታት ወዲህ በገጠማት መከፋፈል ህልውናዋ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ወድቋል፡፡ ይህ ችግር ባህር ተሻግሮ በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ እንዲሁም ኢትዮጵያውያን በስደት በሚኖሩባቸው ሌሎች አካባቢዎች ተባብሶ ይታያ

፡፡ ለምሳሌ እኛ በምንኖርበት ፍራንክፈረትና አካባቢዋ ለአንድ መንፈሳዊ ግልጋሎች ወደ ቤተክርስቲያን ከማቅናትዎ በፊት በጭንቅላተዎ ሳይፈልጉ የሚመላስ ጥያቄ አለ፡፡ ይኸውም ቤተክርስቲያን በሀገር ውስጥ ፣ በውጪው ፣በገለልተኛው ወይስ በኤርትራ በሚመራው ሲኖዶስ ስር ስለመሆኑ ማጣራት ተገቢ ነው፡፡አለበለዚያ በሰላይነት ተጠርጥረው ለግልምጫ ከፋም ሲ

ለዘለፋ ሊዳረጉ ያችላሉ፡፡

 

በኢትዮጵያ ኦ//ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል እርቀሰላም ለማውረድ በ3 ዙር የተካሄደው ውይይት ብዙም ተስፋ ሰጪ ነገሮች ሳይታይበት ለ4ኛ ዙር በተቀጠረበት ባሁኑ ጊዜ በመንግስት ጣልቃገብነት ምክንያት እርቀሰላሙ ችግር ገጥሞታል፡፡ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ ሲጠቀሙበት የነበረውና በቅርቡ በጀነራሎች ሹመት ተግባራዊ ያደረጉት የአንድ ብሄር ጽንፍ የበላይነት ባለፉት ትቂትዓመታት ስር በሰደደ መልኩ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ እየፈጸሙት ይገኛሉ፡፡ ይኸውም በአምስተኛው ፓትሪያርክ የስልጣን ዘመን የሊቃነጳጳሳት፣የጳጳሳት እንዲሁም ከፍተኛ የቤተክርስቲያን አስተዳደር እርክን ላይ አንድ ብሔር ላይ ያተኮረ ሹመት ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል፡፡እነዚህ ተሿሚዎች ቤተክርስቲያን ትታወቅበት የነበረውን ሰላም ፍቅር አንድነት በማጥፋት በምትኩ ጠብ፣ጥላቻ፣ተንኮል ሙስና ለስልጣን እሽቅድምድምና እና ብሄርተኝነት እንዲሰፍን አድርገዋል፡፡እርቀሰላሙ ምንም አይነት መቋጫ ሳይበጅለት ከመንግስት ጎን በመቆም 6ኛ ፓትሪያርክ አስመራጭ ኮሚቴ አዋቅረው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡

በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ አጥቢያ ቤተክርስቲያን እርቀሰላሙን በተመለከተ መግለጫዎች እንዲሁም የተማጽኖ ደብዳቤዎች ቢያጎርፉም እስከ አሁን ድረስ ምእምናኑን የሚያረጋጋ ተስፋ የሚሰጥ ነገር አልታየም፡፡ለእርቀሰላሙ ድርድር ላይ ያሉት ሁለቱ ሲኖዶሶች የባቢሎን ቋንቋ እስኪመስል ድረስ ፍጹም መግባባት መደማመጥ ተስኗቸዋል፡፡ዛሬ ቤተክርቲያናችን በከፍተኛ ሁኔታ ታውካለች፡፡ለነገሩ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራውን ቅዱስ ሲኖዶስ የህወአት መስራቾቹ አቦይ ሰብሀት ነጋ እና አቶ አባይ ጸሀዬ እየመሩት እንዴት ሰላምና አንድነት ይጠበቃል፡፡በህገመንግስቱ አንቀጽ 11 ቁጥር 3 “መንግስት በሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም “በሚለው መሰረት መንግስት ከቤተክርስቲያን ላይ እጁን ያንሳልን፡፡እርቀሰላሙ ቀጥሎ የቤተክርስቲያናችን አንድነት ተመልሶ እንዲመጣ ሁሉም አባቶች እርቀ ስላሙን ተቀብለው እንድ ሁነው አንድ እንዲያደርጉን ደግመን ደጋግምን እንጠይቃልን፡፡

በአንድ ወቅት ሰውየው ስለቱ ከደረሰለት ለሰይጣን/ዲያቢሎስ ጋቢ አሰርቶ ለማልበስ ይሳላል፡፡ባጋጣሚ ስለቱ ይደርስለታል፡፡ ነገር ግን ያሰበው ሰይጣን/ዲያቢሎስን/ በአካል አግኝቶት ማልበስ አልቻለም፡፡ብዙ ካወጣ ካወረደ በኋላ ወደ አንድ አባት ጋር ሂዶ እንዲህ አላቸው፡፡አባቴ ስለቴ ከደረሰልኝ ለሰይጣን/ዲያቢሎስን/ ጋቢ አሰርቼ ለማልበስ ተስዬ ነበር፡፡ስለቴም ሞላልኝ ነገር ግን ሰይጣን/ዲያቢሎስን/ አግኝቼ ማልበስ አልቻልሁም ምን ይሻለኛል በማለት ጠየቃቸው ፡፡እኝህም አባት አይ ልጀ ልብ ሳትል ቀርተህ ነው እንጅ እሱማ በየትም ቦታ ሞልቶልሀል ፡፡ አሁን እንግዲህ አድርግ በመንገድህ ላይ ሰዎች ተጣልተው ሽማግሌዎች ተሰብስበው በአስታራቂነት ተቀምተው ሽምግልናውን(እርቀሰላሙን) አንቢኝ አሻፈረኝ ብሎ እረግጦ የሚሄድ ካለ እርሱ ሰይጣን(ዲያቢሎስ) ነው ፡፡ ጋቢውን ለእርሱ አላብሰው አሉት፡፡ሰውየውም አንደተባለው አደረገ፡፡

እኔ እንደወደድሁዋችሁ እርስበርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትዕዛዜ ይህቺ ናት፡፡ዮሐ.1512 በሚለው መሰረት ሁለቱም ሲኖዶሶች በመካከላቸው እየገባ የሚያሰናክላቸውን ሰይጣን (ዲያቢሎስን) አሳፍረው ከላይ የተጠቀሰውን የባለ ስለቱን ታሪክ በእናንት በአባተች ላይ ተግባራዊ እንዳይሆን እርቀ ስላሙን ተቀብላችሁ አንዲት ቀደምት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሀይማኖትን የቀደመ ስሟን ፣ሰላሟን እና አንድነቷን እንድትመልሱ በእግዚያብሔር ስም እንጠይቃለን፡፡

እግዚያብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባርክ

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close