ግፍ መሸከም በቃኝ!

 

 Mekonnen Workineh, Norway, Oslo.

March.27.2013

ግራ ጎኔ ቆስሎ ቂም አርግዞ ሲመግል፤

መዳኒት አዋቂ ስር ማሽ ቅጠል በጣሽ ጠፍቶ ደረስኩ የሚል።

አማራ ጠላት ነው ብሎ ሰይሞልኝ ነጻ አውጭው የትግሬ፤

መቀመጫ አጣሁ አሜከላ ሆኖ ሳር ምድሯ አገሬ።

አንገቴን ደፍቼ ኑሮ ልግፋ ባልኩኝ፤

ወለጋ ሲዳሞ ለቀን ስራ ሄጄ ቡና በለቀምኩኝ፤

ጎጆዬን ቀልሼ ኑሮዬን መስርቼ ማስኜ በኖርኩኝ።

ደንብሮ እንደወጣ እንደ ጫካ አውሬ፤

ለምንስ ልደብደብ ለምንስ ልሳደድ ከገዛ ሐገሬ።

የትግሬ ነጻ አውጭ ተከዜን ተሻግሮ ጎንደሬውን ፈጅቶ መሬቱን ሲወረው፤

ወደ ደቡብ ሰፍቶ ወሉን ሲያስብረው፤

አፋር ኦጋዴኑን ኦሮም ደቡቡን፤ አኛክ ዳሰነቹን ደርሶ ሲያሸብረው፡

መታደን ያለበት ወንጀለኛው ማን ነው?

አረ አንቀጠቀጠኝ ብርዱ ሆዴ ገባ፤

ህጻን ልጄ ሲወድቅ እያለኝ አባባ፤

ማንሳት እንኳ አቅቶኝ እጄ ሆኖ ሽባ።

እኔ መስሎኝ ነበር ትግሬ ወገኔ ነው፤

አኔ ብዬ ነበር ትግሬ ወንድሜ ነው፤

ነጻ አውጭው ሲፈጀኝ ተው አላለ ምነው?

ሰው በማንነቱ ሰው በዘሩ ሲፈጅ ሰምቼ ነበረ ታሪኩን እንደቀልድ፤

አሁን ባይኔ አየሁት የትግሬ ነጻ አውጭ ነፍሰ ጡር ጥሎ ሲያርድ።

ቁልጭ ብሎ ሚታይ ፍንተው ያለው እውነት፤

የትግሬ ነጻ አውጭ ፍጹም አይፈልግም አማራን ለማየት፤

ቀን ከሌት ይሰራል ኢትዮጵያን ለማጥፋት፡

እኔ ወይ ወያኔ ማ መጥፋት አለበት?

ሐገሬ ተራራው ስርጡ ተረተሩ፤

ክትክታ አጋሙ አሸዋ ኮረቱ

ሁሉም መሣሪያ ነው ስትቆርጥ ልቢቱ።

እኔም ሰው ነኝ እኮ ይከፋኝ ያመኛል፤

በደል እስከመቼ ይታዘልልኛል።

በገዛ ሐገሬ አትኖርም ስባል፤

እንደ ልፋጭ ስጋ ተቆርጬ ስጣል።

ትከሻ የለኝም ይህን የሚሸከም፤

ተናንቄ ልሙት ትንፋሼም ትጨልም።

የትግሬ ነጻ አውጭ ጥንስሱ እየፈላ፤

አላስቀምጥ አለኝ ግማቱ እያስጠላ።

በቃኝ በቃኝ በቃኝ ሸክም በዝቶብኛል፤

ይህ አንገቴን መድፋት ለዚህ አብቅቶኛል፡

ልጄንም ሚስቴንም ማዳን አቅቶኛል፤

የትግሬ ነጻ አውጭ በጠራራ ፀሃይ እኔኑ ደፍሮኛል፡

አገር አገር ብዬ ጥቃቴን ባፍነው፤

የትግሬ ነጻ አውጭ ፈነጨብኝ ምነው?

አባባ ዳቦ ሲል የምሰጠው የለኝ፤

ወንድም ጋሼ ስትል እቴን መች አስጣልኩኝ።

ልጄም እንዳሻህ ሁን አህቴም እንደዛው፤

የትግሬ ነጻ አውጭን ሄጄ ልፋለመው።

ጃሎ በል ወገኔ ወርደህ በለው በለኝ፤

የባንዳ ጥራጊ ከትቢያ ሲቆጥረኝ።

አንደበትም የለኝ አልናገር ዳግም፤

ሰው እስክሆን ድረስ አደባባይ አልቆም፤

የባንዳን ጥራጊ በፍልሚያ ገጥሜ፤

ሰው ሆኜ መጣለሁ ሲያገግም ህመሜ።

ከመኖሪያ ቄያቸው በመሳደድ፤ በመታደን፤ በመገደል ላይ ላሉ አማርኛ ተናጋሪ እትዮጵያውያን እና ሲጓጓዙ መኪና ተገልብጦ ላለቁ እና አሰከሬናቸውን አውሬና አሞራ ለተቀራመተው ወገኖቼ መታሰቢያ ትሁንልኝ

 

Advertisements
%d bloggers like this:
search previous next tag category expand menu location phone mail time cart zoom edit close