Search

AFRO ADDIS

An Inspiring Voice against Despots!

! …. ትንሽ ስለ ጀዋር መሓመድ ……!

 

 

አንድ ጓደኛየ አንድ የተቀናበረ ቪድዮ በፌስቡክ ገፄን ለጠፈልኝ፤ እንዳነበው እየጋበዘኝ መሆኑ ነው። ቪድዮው ስለ ጀዋር ነው። ግን የሌሎች ሰዎች ስሞችም (የኔን ጨምሮ) ተጠቅሷል። ልጁ ቪድዮውን ሲጋብዘኝ አንዳንድ ዲያስፖራ ተቃዋሚዎች ስለኔ ያላቸው አመለካከት እንዳውቅና ኢህአዴግ መቃወሜን እንዳቆም ‘በአሪፍ’ ተፅዕኖ ማሳደሩ ነው፤ ይህን ድምዳሜ የመጣልኝ ልጁ (ቪድዮው የላከልኝ) ከዚህ በፊት ይልክልኝ በነበሩ ተመሳሳይ መልእክቶች በመነሳት ነው። ይህን የፖለቲካ ስትራተጂ እንደማይሰራ በተደጋጋሚ ለማረጋገጥ ሞክርያለሁ።

ግን … Continue reading “! …. ትንሽ ስለ ጀዋር መሓመድ ……!”

Advertisements

“አማራው ያሬድ አይቼህ” ደግሞ ምን ፍጠሩ እያለን ይሆን?

Ethiopia_TFP
Ethiopia_TFP (Photo credit: aheavens)

 

 

                                                                                                      ብሥራት ደረሰ

 

 

 

አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል፡፡  የወደቀም ግንድ ምሣር ይበዛበታል፡፡ ኢትዮጵያም ቀን ጣላትና፣ ቀን ጣላትናም በጠላቶቿ እጅ ወደቀችና፣ በጠላቶቿ እጅ ወደቀችናም የድፍን ስድና መረን ያደገ ዋልጌ ሁሉ የስድብና የዘለፋ አፍ ማሟሻ የመሆን ዕጣ ደረሳትና ይሄውላችሁ በየቀኑ ተነግሮ የማንሰማው ተጽፎም የማናነበው ነገር የሌለን ሆነን ዐረፍነው፡፡ የገዛ ልጆቿም እየከዷት አንዱ ወግጂልኝ ይላታል ሌላው ለርሷ ለመሞት ቆርጦ ተሰልፎላታል፡፡ ደርግ ጥሩ አማርኛ ነበረቺው፡- ‹የእናት ጡት ነካሽ› የምትል፡፡ ዛሬ ዛሬማ የእናት ጡት ነካሽ ብቻ ሳይሆን ባት ቆራጭም፣ ማጅራት ገትርም ማለቴ ማጅራት መቺም፤ አነጣጥሮ አናት በርቋሽም ልጅ ሞልቶናል – የልጅ በያይነቱና ማኅበራዊ በብፌ መልክ በሽበሽ ብሎ ፊታችን ላይ ተዘርግቶልናል (የምግብ ስሞች ናቸው)፡፡ Continue reading ““አማራው ያሬድ አይቼህ” ደግሞ ምን ፍጠሩ እያለን ይሆን?”

Eritrean diplomat ordered out of Canada after ‘tax’ on ex-pats

Eritrean consul general must leave by June 5 CBC

http://www.cbc.ca/player/News/Canada/ID/2386775538/

The head of the Eritrean Consulate in Toronto has been ordered to leave Canada in the wake of reports that said Semere Ghebremariam O. Micael has been involved in soliciting a “diaspora tax” from Eritreans in Canada.

Foreign Affairs Minister John Baird issued a news release Wednesday that said he has taken steps to expel Micael and he must leave by noon ET on June 5.

“Today’s actions speak for themselves,” Baird said. “Canada has repeatedly made clear to Eritrea to respect international sanctions and Canadian law.” Continue reading “Eritrean diplomat ordered out of Canada after ‘tax’ on ex-pats”

በኢትዮ ኬኔያ ድንበር ላይ ውጥረቱ አይሏል ታጣቂዎች 3ሰዎችን ገደሉ

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ  ግንቦት 11  ቀን 2005 ፕሮግራም

<<አቶ መለስ አንገታቸውን የደፉበት ቀን ቢያንስ ድምጻችንን ያሰማንበት ቀን ነው።ብዙ ሰዎች በየዓመቱ ሊከበር ይገባል ይላሉ።በስርዓቱ ውስጥ የሚታየው የስልጣን ሽኩቻ ተጠናክሮ ይቀጥላል።አውራው አምባገነን ከሞቱ በሁዋላ  አንዱ ገኖ ለመውጣት የሚያደርገው ነው።ሁሉም ቦታው ለኔ ይገባል በሚል ግብ ግባቸው አንዱ አንዱን መክሰሱ አንደኛው ወገን በአሸናፊነት እስኪወጣ ቀጣይ ነው። ወደፊትም አንዱ አንዱን ሲያስር አንዱ ሌላውን ሲከስ እናያለን ።ስርዓቱ ደካማ ነው።የምናየውም የጥንካሬ ምልክት አይደለም…>> ጋዜጠኛ አበበ ገላው አቶ መለስን አንገት ያስደፋበትን የተቃውሞ ድምጹ አንደኛ ዓመትን አስመልክቶ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ ምልልስ የተወሰደ Continue reading “በኢትዮ ኬኔያ ድንበር ላይ ውጥረቱ አይሏል ታጣቂዎች 3ሰዎችን ገደሉ”

ገዳዩ ሞቶ ተገኘ (ማንነቱ እያነጋገረ ነው!)

(ኢ.ኤም.ኤፍ) ከትላንት በስትያ፤ ምሽት ላይ ከ12 ሰዎች በላይ የገደለው የፌዴራል ፖሊስ አባል አባይ ወንዝ ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል። የፖሊሱ ማንነት በውል ባይታወቅም በባህር ዳር ከተማ በሰፊው እየተነገረ ያለው፤ ግለሰቡ የህወሃት አባል እንደሆነና ድርጊቱን የፈጸመው፤ ሆን ብሎ በአማራ ህዝብ ላይ ያለውን ጥላቻ ለመግለጽ ነው፤ የሚለው ወሬ በሰፊው እየተናፈሰ ይገኛል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በፌዴራል ፖሊስ ሰበብ በከተማው በሚገኙት የሌላ ብሄር ተወላጆች ላይ ህዝቡ ቁጣውን እየገለጸ ነው። ይህንን የህዝብ ስሜት ለማብረድ እና ለማባበል በሚመስል መልኩም የፌዴራል ፖሊስ በተደጋጋሚ ይቅርታ እየጠየቀ ነው።

ገዳዩ የፌዴራል ፖሊስ ከአባይ ወንዝ ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል

ገዳዩ የፌዴራል ፖሊስ ከአባይ ወንዝ ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል
ከትላንት በስትያ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ላይ በተፈፀመው ድርጊት ከሞቱት መካከል ሴቶች ፣ ህፃናትና  አዛውንቶች ይገኙበታል ። ከተገደሉት ግለሰቦች መካከልም የሰባቱ የቀብር ስነ ስርዓት በደብረ አባይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን በጋራ  ተፈፅሟል ።
በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ  የተገኙት የአማራ  ክልል  ርእሰ መስተዳድር  አቶ አያሌው ጎበዜ የክልሉ መንግስት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተዋል ።
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን  በበኩሉ በግለሰቡ ድርጊት ህይወታቸውን ባጡ ዜጎች  ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል ፡፡

 

በእንዲዚህ አይነቱ  ወንጀልም በህብረተሰቡና በፖሊስ መካከል ለዓመታት የቆየው መልካም ግንኙነትም አይሻክርም ብሏል በመግለጫው፡፡

የፖሊስነት ሙያዊ ዲስፕሊን  በጎደላቸው መሰል ፖሊሶችም ይህ አይነት ክስተት ደግም እንዳይፈጠር ጥረት እንደሚያደርግ ገልጿል። ይህ ሁሉ የፌዴራል ፖሊስ ልመና ግን ለህዝቡ እምብዛም የተዋጠለት አይመስልም። ይልቁንም ሰሞኑን በህወሃት ውስጥ የተፈጠረው ሽኩቻ ያበሳጨው ሰው መሆኑ ነው በሰፊው የሚወራው። ፖሊስም ይህንን የህዝቡን ቁጣ ላለማባባስ ሲል፤ የገዳዩን ስም እና ማንነት ከመግለጽ ተቆጥቧል፡፡

Create a free website or blog at WordPress.com.

Up ↑

%d bloggers like this: